ኢትዮጵያ ከሶማሊያና ከደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክና የመንገድ ትስስር ልትፈጥር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
12:01 01.02.2026 (የተሻሻለ: 12:04 01.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከሶማሊያና ከደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክና የመንገድ ትስስር ልትፈጥር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ዕቅዱን በስኬት ለማጠናቀቅ በኢትዮጵያ እንዲሁም በሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን በኩል አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ከሱዳን፣ ኬንያና ታንዛኒያ ጋር በኤሌክትሪክና ሌሎች ዘርፎች በትብብር እየተሠራ መሆኑንም ጨምረው ጠቁመዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
የኢትዮጵያ እድገትና ኢነርጂ ከአካባቢው ሀገራት ትስስር ውጪ ለብቻ በማደግ የሚረጋገጥ አለመሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X