አሜሪካ የምታሸማግለው ቀጣዩ የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር በዛሬው ዕለት በአቡ ዳቢ ይካሄዳል፦ ቁልፍ ጉዳዮች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ የምታሸማግለው ቀጣዩ የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር በዛሬው ዕለት በአቡ ዳቢ ይካሄዳል፦ ቁልፍ ጉዳዮች
አሜሪካ የምታሸማግለው ቀጣዩ የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር በዛሬው ዕለት በአቡ ዳቢ ይካሄዳል፦ ቁልፍ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.02.2026
ሰብስክራይብ

አሜሪካ የምታሸማግለው ቀጣዩ የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር በዛሬው ዕለት በአቡ ዳቢ ይካሄዳል፦ ቁልፍ ጉዳዮች

◻ ውይይቱ በግዛት ጉዳዮች እና በዛፖሮዢያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ዙሪያ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል።

◻ የዩክሬን ኃይሎች ከዶንባስ መውጣት ለሩሲያ ወገን ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ክሬምሊን ቀደም ብሎ ቢገልጽም፤ ዩክሬን በዶንባስ እና በኒውክሌር ጣቢያው ጉዳይ ለመመቻመች ዝግጁ አለመሆኗን ዘለንስኪ ዓርብ ተናግሯል።

◻ የልዑካን ቡድኑ ተሳታፊዎች እስካሁን አልታወቁም። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሁለተኛው ዙር ውይይት የሁለትዮሽ እንደሚሆንና የአሜሪካ ተሳትፎ ሊኖር እንደሚችል ቢገልጹም፤ የትራምፕ መልዕክተኛ ዊትኮፍም ሆኑ ኩሽነር በውይይቱ ላይ አይገኙም።

◻ የመጀመሪያው የሦስትዮሽ ስብሰባ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአቡ ዳቢ ተካሂዷል፡፡ ሩሲያን የወታደራዊ ደህንነት ኃላፊው ኢጎር ኮስትዩኮቭ ሲወክሉ ዩክሬን ደግሞ በመከላከያ ምክር ቤት ፀሐፊው ሩስተም ኡሜሮቭ ተወክላለች።

◻ እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጻ፤ ውይይቱ የአሜሪካን የሰላም ዕቅድ ያልተቋጩ ነጥቦች እና መተማመኛ እርምጃዎችን ዳስሷል።

ለመጀመሪያው ዙር ድርድር የተሰጡ ምላሾች፦

ክሬምሊን በጉዳዩ ውስብስብነት ምክንያት ትልቅ ውጤት አይጠበቅም ያለ ሲሆን ሆኖም ቀጥተኛ ንግግር መጀመሩን በበጎ ተመልክቶታል።

የሩሲያ ተደራዳሪ ኮስትዩኮቭ፤ ከዩክሬን ጋር የተደረገው ንግግር በሩሲያኛ ቋንቋ መካሄዱን ጠቅሰው፤ “በጣም አስፈላጊ ነገሮች የሚወሰኑት በዝምታ ነው” ብለዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ድርድሩ በሚስጥር መያዝ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው፤ ሩሲያ በማንኛውም መንገድ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውይይቱ ድባብ ገንቢ እና አወንታዊ እንደነበር ገልጻለች።

ኋይት ኅውስ ውይይቱን “ታሪካዊ” ሲል ጠርቶታል፡፡ ትራምፕ በበኩላቸው “በጣም ጥሩ ነገሮች” እየተከናወኑ መሆናቸውን እና የዩክሬን የሰላም ስምምነት "በቅርቡ ይሳካል" የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0