ሽብርተኝነት እና ፀረ ሽብርተኝነት አሜሪካ ለምትፈፅማቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች መግቢያ ናቸው - የጅኦግራፊ ባለሙያ
10:02 01.02.2026 (የተሻሻለ: 10:04 01.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሽብርተኝነት እና ፀረ ሽብርተኝነት አሜሪካ ለምትፈፅማቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች መግቢያ ናቸው - የጅኦግራፊ ባለሙያ
አሜሪካኖቹ የሚፈልጉት ሀገራትን መንግሥታት አዳክመው እና ከፋፍለው በመግዛት፣ አሻንጉሊት የሆኑ መንግሥታት የመትከል እና ቀጣናውን ማተራመስ ነው ሲሉ የጂኦግራፊና የካርታ ሥራ ባለሙያው መሐመድ ንጉሥ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
መሐመድ፣ አሜሪካኖች ፖሊሲአቸውን መካከለኛው ምስራቅ ለመበታተን ላለፉት 50 ዓመታት ከዛ በላይ ተጠቅመውበታለ ሲሉ ገልፅዋል፡፡
"ቶኒ ብሌር በግልፅ በሕይወታቸው የሚቆጩት ኢራቅ ላይ በወሰዱት እርምጃ ነው... አሁን በኢራን ላይ የሚጠነሰሰው ሴራ ተመሳሳይ ስህተት ነው። ፖሊሲውም ተመሳሳይ ነው" በማለት ባለሙያው የአሜሪካ መሪዎች የድሕረ-ስልጣን ፀፀት እና የፖሊሲውን ተድጋጋሚ ውድቀት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሀገሪቱ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያላት ተቀባይነት ወይም ተጽዕኖ እንደ ድሮ አይደለም ሲሉም ይሞግታሉ።
የጂኦግራፊና የካርታ ሥራ ባለሙያው "ከእስራኤል ጋር በነበረው የ12 ቀን ጦርነት ራሷን ለመከላከል ኢራን የወሰደችው እርምጃ ጉልበቷ፣ ኃይሏ በቀላሉ [...] መፍረስ እንደማትችል አሳይታለች" ሲሉም የኢራንን ተሞክሮ በቀጣናው ላይ የእምቢተኝነት ተፅዕኖ መፍጠሩን አስረድተዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X