ዚምባብዌ እና ሩሲያ 45ተኛ ዓመት የግንኙነት በዓል አስመልክተው ትስስራቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አምባሳደሩ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዚምባብዌ እና ሩሲያ 45ተኛ ዓመት የግንኙነት በዓል አስመልክተው ትስስራቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አምባሳደሩ ገለጹ
ዚምባብዌ እና ሩሲያ 45ተኛ ዓመት የግንኙነት በዓል አስመልክተው ትስስራቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አምባሳደሩ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.01.2026
ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ እና ሩሲያ 45ተኛ ዓመት የግንኙነት በዓል አስመልክተው ትስስራቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አምባሳደሩ ገለጹ

ማዕድን ልማት፣ ጤና፣ ትምህርት እና ሌሎችም ዘርፎች የትብብሩ መሠረት መሆናቸውንም በሀራሬ የሞስኮ አምባሳደር ጨምረው ገልፀዋል።

​ የዚምባብዌ "የነባር ግንኙነት እና የታደሰ ዳግም ግንኙነት" የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከሞስኮ ጋር ያለውን የቆየ ስልታዊ አጋርነት እያሳደገው መሆኑን በሀራሬ የሩሲያ አምባሳደር ኒኮላይ ክራሲልኒኮቭ ለዚምባብዌ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

​ዲፕሎማቱ ሁለቱ ሀገራት በየካቲት ወር የ45 ዓመታት የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ሲያከብሩ፣ ለጋራ ብልጽግና ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የክራሲልኒኮቭ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

በፕሬዝዳንት ፑቲን እና በፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ መካከል ባለው ጠንካራ የጋራ መግባባት ምክንያት ከጎርጎሮሳውያኑ 2017 ጀምሮ ትብብሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

​ ዋና ዋና የትብብር መስኮች ማዕድን ማውጣት (ከሩሲያው ግዙፍ የአልማዝ አምራች አልሮሳ ጋር)፣ ጤና ጥበቃ (ብሔራዊ የአየር አምቡላንስ አገልግሎትን ጨምሮ) እና ትምህርትን ያካትታሉ፡፡

​ የዚምባብዌ “ለንግድ ክፍት የመሆን” ፖሊሲ ለኢኮኖሚያዊ ትስስሩ መጠናከር እንደ ትልቅ መነቃቂያ ተጠቅሷል፡፡

​ የጋራ ፕሮጀክቶችን ወደፊት ለማራመድ፣ በዚህ ዓመት ዚምባብዌ ውስጥ የፍተኛ ደረጃ የሁለትዮሽ ኮሚሽን ስብሰባ ለማካሄድ ታቅዷል፡፡

​ ሞስኮ፣ ሀራሬን ለወደፊቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ እንደ አንዷ ጠንካራ አስተናጋጅ ሀገር ትመለከታታለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0