የአሜሪካው ዳኛ የኢትዮጵያውያንን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ የሚያነሳውን ውሳኔ አገዱ
17:50 31.01.2026 (የተሻሻለ: 17:54 31.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካው ዳኛ የኢትዮጵያውያንን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ የሚያነሳውን ውሳኔ አገዱ
በትላንትናው ዕለት፣ በአሜሪካ የቦስተን አካባቢ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የከለላ ደረጃ (ቲፒኤስ) ለማቋረጥ የወሰነውን እና የካቲት 3 ተግባራዊ የሚሆነውን ቀነ-ገደብ የሚያዘገይ ትዕዛዝ እንደሰጡ ገልጸዋል።
ዳኛው በበየነ መረብ ችሎት ላይ እንደተናገሩት፣ የውሳኔው መዘግየት ሚኒስቴሩ ውሳኔውን እንዴት እንዳስተላለፈ ዝርዝር መዝገቦችን እንዲያቀርብ ጊዜ ይሰጣል። ዳኛው እነዚህን ሰነዶች ከተመለከቱ በኋላ ውሳኔውን ለረጅም ጊዜ ማገድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ መናገራቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከቀናት በፊት የትራምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያውያን የጥበቃ መብት ያነሳው "በዘር ጥላቻ ላይ ተመሥርቶ ነው" የሚል ክስ እንደተመሠተበት ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X