ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶች እገዳን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፤ ከባድ የገንዘብ ቅጣትም ተጥሏል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶች እገዳን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፤ ከባድ የገንዘብ ቅጣትም ተጥሏል
ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶች እገዳን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፤ ከባድ የገንዘብ ቅጣትም ተጥሏል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶች እገዳን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፤ ከባድ የገንዘብ ቅጣትም ተጥሏል

ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የማስገባት፣ የማምረት እና ለንግድ ሥራ የመጠቀም  አገር አቀፍ እግድ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ይህ እርምጃ ከፍተኛ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የታለመ ሲሆን፣ ለ6 ወራት ተሰጥቶ የነበረው የቅድመ ዝግጅት ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ ሕጉን በሚጥሱ አካላት ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ይጣላል ተብሏል።

ቅጣቱም እንደ ጥፋቱ ደረጃ የሚለያይ ሲሆን፣ ለተጠቃሚዎች ከሁለት ሺህ ብር ጀምሮ ለአቅራቢዎች፣ ለአምራቾች እና አስመጪ ድርጅቶች ደግሞ ከ50 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ይደርሳል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0