ሩሲያ ለኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ጥቃትን የዩክሬንን ብቸኛ ተጠያቂነት ውድቅ አድርጋለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
18:35 30.01.2026 (የተሻሻለ: 18:44 30.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ጥቃትን የዩክሬንን ብቸኛ ተጠያቂነት ውድቅ አድርጋለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
በኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ለተፈፀመው ጥቃት "በብቸኝነት ዩክሬናውያን ብቻ ተጠያቂ " ናቸው በሚል ዓለምን ለማሳመን የሚደርገውን ሙከራ ሩሲያ እንደማትቀበለው ማሪያ ዛካሮቫ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
"ገለልተኛ እና አጠቃላይ ምርመራ የማካሄድ ተግባር አሁንም በአጀንዳነት እንደቀጠለ ነው" ያሉት ቃል አቀባይዋ፣ "የምዕራባውያን የመረጃ ድርጅቶች እጅ አለበት የሚለው መላምት ተገቢው ማረጋገጫ ያስፈልገዋል" ብለዋል።
በጥር ወር መጀመሪያ የጀርመን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2022 የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያዎች ላይ በቦምብ ጥቃት ፈፅሟል በሚል የሚጠረጠረውን ሰርሂ ኩዝኔትሶቭ የተባለ የዩክሬን ዜጋ እስር አፅንቷል።
ፍርድ ቤቱ ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው ምናልባትም የአንድ የውጭ አገር መንግሥት ትዕዛዝን በመቀበል ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
በኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ምን እንደተከሰተ የስፑትኒክ አፍሪካን ዝርዝር ዘገባ ያንብቡ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X