ናሚቢያ የረጅም ጊዜ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒትን አፀደቀች፤ ተደራሽነቱንም ለማረጋገጥ ቃል ገብታለች - ሚኒስቴር

ናሚቢያ የረጅም ጊዜ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒትን አፀደቀች፤ ተደራሽነቱንም ለማረጋገጥ ቃል ገብታለች - ሚኒስቴር
የናሚቢያ መንግሥት አዲሱን የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት ሌናካፓቪርን መመዝገቡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በዚህም ናሚቢያ በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በክትባት መልክ የሚሰጠውን ይህን መድኃኒት በማጽደቅ ከመጀመሪያዎቹ የአፍሪካ አገራት ተርታ ተሰልፋለች።
ይህ እርምጃ በየቀኑ ከሚወሰዱ ክኒኖች ይልቅ አማራጭ በማቅረብ፣ አገሪቱ ለኤችአይቪ የምትሰጠውን ምላሽ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ክትባቱን የተመለኩቱ ዝርዝር መረጃዎች፦
መድኃኒቱ በዓመት ሁለት መርፌዎችን ብቻ የሚፈልግ በመሆኑ፣ በየቀኑ መድኃኒት ከመውሰድ ጋር ሲነፃፀር ለታካሚዎች ምቹ ሊሆን ይችላል።
ባለሥልጣናት መድኃኒቱ በአሁኑ ወቅት በአንድ ሰው በዓመት ከ28 ሺህ ዶላር በላይ የሚጠይቅ ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው ቢገነዘቡም፣ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራቸው መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
መንግሥት ለሕዝብ ጤና ፕሮግራሞች እንዲውል ዋጋው እንዲቀነስ በ“አፍሪካ መድኃኒቶች ኤጀንሲ” በኩል ግፊት እያደረገ ይገኛል።
ናሚቢያ ምንም እንኳን አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ባይቆምም፣ የተባበሩት መንግሥታት የኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮግራም (UNAIDS) የሕክምና ግቦች ካሳኩ አገራት አንዷ መሆኗ ይታወሳል።
ይህ ምዝገባ ከጎረቤት አገራት ደቡብ አፍሪካ እና ዛምቢያ ጥረቶች ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ በቀጣይ ትውልድ የኤችአይቪ መከላከያ መሣሪያዎች አጠቃቀም ረገድ ቀጠናዊ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X