በኒያሜ አየር ማረፊያ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት - ቲያኒ ለኒጀር ባላቸው የጠላትነት አቋም የሚታወቁ አገራት መሪዎችን ወነጀሉ
17:26 30.01.2026 (የተሻሻለ: 17:34 30.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኒያሜ አየር ማረፊያ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት - ቲያኒ ለኒጀር ባላቸው የጠላትነት አቋም የሚታወቁ አገራት መሪዎችን ወነጀሉ
የዲዮሪ ሃማኒ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ “በርቀት በሚታዘዙ ቅጥረኞች የመግባት ሙከራ ተደርጎበታል” ሲሉ የኒጀር ፕሬዝዳንት በጥር 20 እና 21 ምሽት ጥቃት የደረሰበትን ተቋም በጎበኙበት ወቅት ገልጸዋል።
አብዱራሃማኔ ቲያኒ ባደረጉት ንግግር፣ “ለእነዚህ ቅጥረኞች ስፖንሰር ለሆኑት ማለትም ለኢማኑኤል ማክሮን፣ ለፓትሪስ ታሎን እና ለአላሳኔ ኦዋታራ ለረጅም ጊዜ ሲጮኹ እንደሰማናቸው አስታውሰናቸው፤ አሁን ደግሞ የእኛን ግሣት ለመስማት ይዘጋጁ” ብለዋል።
ሀገሪቱ መሪ ጥቃቱን በመመከት ረገድ ለተሳተፉት የኒጀር መከላከያ እና የደህንነት ኃይሎች እንዲሁም ለ“ሩሲያ አጋሮቻቸው” ምስጋና አቅርበዋል።
ጥቃቱን አስመልክቶ የተሰጡ ዝርዝር መረጃዎች፦
▪የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴር 20 ትቃት ፈጻሚዎች መገደላቸውንና ሌሎች 11 በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
▪ጥቃቱ የተፈጸመው “መብራታቸውን ባጠፉ ሞተር ብስክሌቶች በታጀቡ አጥቂዎች” አማካኝነት ነው።
▪አራት የኒጀር ወታደሮች የቆሰሉ ሲሆን፣ የእሳት አደጋ የደረሰበትን የጥይት ማከማቻ መጋዘንን ጨምሮ በሌሎች ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X