ይመልከቱ | የሩሲያ መኮንን ለመግደል አቅዶ የነበረውና ከዩክሬን ጋር ግንኙነት ያለው ወኪል በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ቁጥጥር ስር ዋለ

ሰብስክራይብ

ይመልከቱ | የሩሲያ መኮንን ለመግደል አቅዶ የነበረውና ከዩክሬን ጋር ግንኙነት ያለው ወኪል በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ቁጥጥር ስር ዋለ

​የሩሲያ የደህንነት ተቋም (ኤፍኤስቢ) በዩክሬን ልዩ አገልግሎት ስምሪት አንድን የሩሲያ ወታደራዊ መኮንን ለመግደል አቅዶ የነበረን ግለሰብ በዛሬው ዕለት በሴንት ፒተርስበርግ በቁጥጥር ስር አውሏል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

​▪ ተጠርጣሪው በቴሌግራም አማካኝነት ከቀጣሪው  ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለዩክሬን ድጋፍ የሚሆን የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ተስማምቷል።

▪ ከበላይ ተቆጣጣሪው መመሪያ በመቀበል፣ ድምፅ ማፈኛ ያለው የማካሮቭ ሽጉጥ ታጥቆ የጥቃቱ ኢላማ የሆነው ግለሰብ መኖሪያ አካባቢ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ አከናውኗል።

▪ ሊገደል የታቀደው ግለሰብ "ወታደራዊ መኮንን፣ ምናልባትም ሌተናል ኮሎኔል" እንደሆነ ተገልጿል።

▪ የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት፣ ግለሰቡ ተልዕኮውን የጀመረው ለገንዘብ ክፍያ እንደሆነ ሲናዘዝ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ለቋል።

▪ በሽብር ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0