የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ቅርሶች በሩሲያ መንግሥት የታሪክ ቤተ-መጻሕፍት ለዕይታ ቀረቡ
15:21 30.01.2026 (የተሻሻለ: 15:24 30.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ቅርሶች በሩሲያ መንግሥት የታሪክ ቤተ-መጻሕፍት ለዕይታ ቀረቡ
“ከክርስትና ምንጮች” የተሰኘ ዐውደ–ርዕይ በትናንትናው ዕለት በሞስኮ ተከፍቷል፡፡
በዐውደ–ርዕዩ ከዓለም ጥንታዊ የክርስትና እምነቶች አንዷ የሆነችውን፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥልቅ ታሪካዊ መሠረቶችን እና ልዩ ጥበባዊ አሻራ ያረፈባቸው ቅርሶችን የሚያሳዩ የቤተክርስቲያን መገልገያ ሀብቶችን ለሕዝብ ዕይታ አቅርቧል።
ይህ ዐውደ–ርዕይ፦
በብራና ላይ የታጻፉ ጥንታዊ የግዕዝ መጻሕፍት፣
ጥበባዊ ይዘት ያላቸው መስቀሎች እና
ቅዱሳት–ሥዕላት ቀርበውበታል፡፡
ይህም ከ4ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የዳበረውን መንፈሳዊ ባህል ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ ለተመልካች ያቀርባል ሲል በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

