ሩሲያ መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ አዲሱን "ሚዛናዊነትን የማስጠበቅ" እና የማረጋጋት ሚናዋን እያጠናከረች ነው - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ አዲሱን "ሚዛናዊነትን የማስጠበቅ" እና የማረጋጋት ሚናዋን እያጠናከረች ነው - ተንታኝ
ሩሲያ መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ አዲሱን ሚዛናዊነትን የማስጠበቅ እና የማረጋጋት ሚናዋን እያጠናከረች ነው - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.01.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ አዲሱን "ሚዛናዊነትን የማስጠበቅ" እና የማረጋጋት ሚናዋን እያጠናከረች ነው - ተንታኝ

​ሊባኖሳዊው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ኤልያስ ሙር፣ ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ እየተቀያየረ ባለው ፖለቲካዊ ገጽታ ውስጥ ወሳኝ የሰላም እና የመረጋጋት ምንጭ በመሆን እየወጣች ነው።

ባለሙያው የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት አሕመድ አል-ሻራ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በቅርቡ በሞስኮ ያደረጉትን ጉብኝት እንደ ማሳያ ይጠቅሳሉ። ይህም የሩሲያ ሚና ከወታደራዊ ተሳትፎ ባለፈ፣ ለድህረ-ግጭት መረጋጋት እንደ መዋቅራዊ ምሶሶ እየታየ መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል።

​"ከዚህ አንጻር ሲታይ፣ አሁን ያለው የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ግጭቶችን ከማባባስ ይልቅ በግጭት አያያዝ ላይ በማተኮር ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማጠናከር የሚደረግ ሰፊ ስትራቴጂ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል" ሲሉ አስረድተዋል።

​ሞስኮ፣ ከቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተዋናዮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ዝግጁ በመሆን፣ ፖለቲካዊ ማዕቀፎችን እንደገና በማመጣጠን፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና በተለይም በኃይል እና በስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑን ሙር አፅንዖት ሰጥተዋል።

​ ተንታኙ ሲያጠቃልሉም፣ ሩሲያ ከባሕረ ሰላጤው አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከሯ፣ አገራቱ በአሜሪካ የአንድ ወገን ውሳኔዎች ያላቸውን ቅሬታ እና አጋርነታቸውን ከሩሲያ እና ከቻይና ጋር ጭምር ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0