ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የአረቢካ ቡና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቁልፍ ምክንያቶችን የለየ ጥናት ይፋ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የአረቢካ ቡና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቁልፍ ምክንያቶችን የለየ ጥናት ይፋ አደረጉ
ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የአረቢካ ቡና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቁልፍ ምክንያቶችን የለየ ጥናት ይፋ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የአረቢካ ቡና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቁልፍ ምክንያቶችን የለየ ጥናት ይፋ አደረጉ

የቡና ምርት ጥራት እንደ አፈር ንጥረ-ነገር የመያዝ አቅም፣ የጥላ ዛፎች መኖር፣ የአፈር እርጥበት እና ናይትሮጅን ባሉ 12 የተቀናጁ ምክንያቶች እንደሚወሰን የአሥር ዓመታት መረጃ ላይ ተንተርሶ በጌዴኦ ዞን የተካሄደው ጥናት አመላክቷል፡፡

ምርቱ ላይ ተፅዕኖ ካላቸው እንደ አካባቢያዊ የመሬት ከፍታ ካሉ ነጠላ ምክንያቶች ባሻገር እነዚህ ምክንያቶች በምርት ሂደት ላይ የሚታየውን 95.4 በመቶ ልዩነት ይወስናሉ ተብሏል።

  ጥናቱ ሁሉንም አካባቢዎች በእኩል የሚመለከት አንድ ወጥ አሰራር ከመከተል ይልቅ፣ እንደየ አካባቢው አየር ንብረት የተለየ ስትራቴጂ መከተል እንደሚገባ ምክረ ሀሳብ አስቀምጧል።

የጥላ ዛፎችን መጠቀምን የመሰሉ ነባርና ዘላቂ የግብርና አሰራሮች የቡናን ጥራት ለመጠበቅ ያላቸውን ፋይዳ ጥናቱ በድጋሚ አረጋግጧል።

የአየር ንብረት መለዋወጥ በአረቢካ ቡና ምርት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ በመሆኑ፣ እነዚህን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች መረዳት የኢትዮጵያን የቡና ኢንዱስትሪ ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።

በ"ቢቬሬጅ ፕላንት ሪሰርች" ጆርናል ላይ የታተመው እና በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተካሄደው ይህ ጥናት፣ ለገበሬዎች፣ ለግብርና ባለሙያዎችና ለፖሊሲ አውጪዎች ምርትንና ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል ተግባራዊ ምክረ-ሐሳብ አቅርቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0