የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቲኑቡ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ይፋ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቲኑቡ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ይፋ አደረጉ
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቲኑቡ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ይፋ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.01.2026
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቲኑቡ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ዕቅድ ይፋ አደረጉ

በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የ10 ዓመት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የኑሮ ማጠናከሪያ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል። ይህም መንግሥት ለዜጎች ክብር ቅድሚያ የሚሰጡ ዘላቂ መፍትሄዎችን ለመተግበር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የፌዴሬሽኑ መንግሥት ዋና ጸሐፊ የሚዲያ አማካሪ ዮሚ ኦዱኑጋ ገልጸዋል።

እንደ ኦዱኑጋ ገለጻ፣ መርሃ ግብሩ በሚከተሉት ዘርፎች ድጋፍ ያደርጋል፦

🟠 የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ ዘመናዊና ግብርና፣  

🟠 የታዳሽ ኃይል የሥራ ዘርፎች፣ 

🟠 የአየር ንብረት መረጃ ነክ የሥራ ዕድሎች፣ 

🟠 የአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረጉ (አረንጓዴ) የንግድ ሰንሰለቶች እና 

🟠 ለሴቶች እና ለወጣቶች የታለሙ የአመራር ሥልጠናዎች።

ፕሬዝዳንት ቲኑቡን ጠቅሰው ኦዱኑጋ እንዳብራሩት፣ ይህ መርሃ ግብር የተቀረጸው ኢኮኖሚያዊ አቅምን መፍጠር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ወሳኝ መሣሪያ ነው በሚል እምነት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0