ኢትዮጵያ የኢነርጂ ውህደት ለአፍሪካ ቀንድ የተሳሰረ ዕድገት እና መረጋጋት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው ገለጸች
17:47 29.01.2026 (የተሻሻለ: 18:24 29.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኢነርጂ ውህደት ለአፍሪካ ቀንድ የተሳሰረ ዕድገት እና መረጋጋት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው ገለጸች
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በሞቃዲሾ በተካሄደው የአፍሪካ ቀንድ ተነሳሽነት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢነርጂ ውህደት ለቀጣናው የያለውን ወሳኝ ጠቀሜታ አጽንኦት በመስጠት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በ2030 ሁለንተናዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳካት፣ ከተለያዩ ምንጮች ከ9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚጠይቀውን "ብሔራዊ የኢነርጂ ኮምፓክት" በአጭሩ አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል በማመንጨትና ቀጣናዊ ትስስርን በማስፋፋት ያሳየችውን እድገትም ጠቅሰዋል።
በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ከጅቡቲ እና ከኬንያ ጋር ካላት ነባር የኤሌክትሪክ መስመር ትስስር በተጨማሪ፣ የልማት አጋሮች ከሶማሊያና ከደቡብ ሱዳን ጋር አዳዲስ ትስስሮችን ፋይናንስ ለማድረግ አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸው ተገልጿል።
ተሳታፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቀጣናው ዘላቂ ልማትን በማጎልበት ያለውን ለውጥ የማምጣት አቅም እውቅና መስጠታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia