ወርቅ ለአፍሪካ የገንዘብ ሉዓላዊነት ዋስትና ሊሆን ይችላል - ናይጄሪያዊው የፖሊሲ አማካሪ

ሰብስክራይብ

ወርቅ ለአፍሪካ የገንዘብ ሉዓላዊነት ዋስትና ሊሆን ይችላል - ናይጄሪያዊው የፖሊሲ አማካሪ

የወርቅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር የደቡብ አፍሪካን የላኪነት ገቢ እያሳደገ እና የሀገሪቱን ገንዘብ (ራንድ) እያጠናከረ ይገኛል፤ ይህም ለአፍሪካ ኢኮኖሚዎች ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ኦቪግዌ እግዌጉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የምርቶች ዋጋ መጨመር የመንግሥታትን የገቢ ምንጭ እንደሚያሳድግ፣ የዋጋ ግሽበትን ጫና እንደሚያቃልል እና በባለሀብቶች ዘንድ እምነትን እንደሚጨምር ጠቁመው፤ ይህም ወርቅን ለደቡብ አፍሪካ እና ለሌሎች ላኪ ሀገራት “እጅግ ተፈላጊ ልማት” እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

ወርቅ “ከሁሉ በላይ እውነተኛ እና የተመሰከረለት የሀብት (እሴት) ማከማቻ” ሆኖ እንደቀጠለ የገለጹት እግዌጉ፣ የአፍሪካ ሀገራት በአሜሪካ ዶላር ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ጥገኝነት እንደገና ሊፈትሹ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይልቁንም በንግድ እና በገንዘብ ፖሊሲ ላይ “በብቃት እና በሉዓላዊነት” ላይ ማተኮር አለባቸው ብለዋል።

እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ያሉ አንዳንድ አምራቾች የሀገራቸውን ገንዘብ ከወርቅ ጋር ማገናኘት የሚችሉበትን መንገድ ማሰብ እንዳለባቸው፣ ሌሎች ደግሞ በተለያዩ የማዕድናት ስብስብ ላይ ሊመሰረቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

እንደ እግዌጉ ገለጻ፣ ምዕራባውያን ሀገራት እንዲህ ያሉ እርምጃዎችን እንደ ጠላትነት ሊመለከቷቸው ቢችሉም፣ ለደቡብባዊው ዓለም ሀገራት ግን ይህ ስለ “ሉዓላዊነት... ስለ ፋይናንስ ብቃት እና ስለ ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ቅልጥፍና” እንጂ ስለ ግጭት አይደለም።

ባለሙያው አክለውም ማሊን፣ ጋናን እና ዚምባብዌን ጠንካራ የሀብት አስተዳደር እንዴት የሀገርን ገንዘብ እንደሚያረጋጋ፣ የዋጋ ግሽበትን እንደሚቀንስ እና ኢንቨስትመንትን እንደሚስብ እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። ዚምባብዌ የሀብት ቁጥጥር እንዴት ኢኮኖሚያዊ ማገገምን እንደሚመራ “አዎንታዊ ምሳሌ” እየሆነች መምጣቷንም ተናግረዋል።

ወደፊትም እውነተኛ የገንዘብ ነፃነት የሚወሰነው በተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት እና አመራር ላይ መሆኑን በማንሳት ይምግታሉ።

“መሠረታዊው ጥያቄ... ገንዘብህን ልታስቀምጥባቸው በምትችላቸው ነገሮች ላይ ሉዓላዊነት አለህ ወይ የሚለው ነው።”

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወርቅ ያለው ፍላጎት መጨመር በተለመዱት የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ ያለውን እምነት መሸርሸር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት ወቅት ወርቅ ያለውን አስተማማኝ የሀብት ማከማቻነት ሚና ዳግም እንደሚያረጋግጥ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0