በሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት መከተባቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት መከተባቸው ተገለፀ
በሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት መከተባቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.01.2026
ሰብስክራይብ

በሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት መከተባቸው ተገለፀ

በአራተኛው ዙር ብሔራዊ ዘመቻ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ሕፃናት አዲሱን የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ማግኘታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ አስታውቋል።

በቤት ለቤት ዘመቻው የሥርዓተ-ምግብ ምርመራ እና የማርበርግ ቫይረስ ክትትልን ጨምሮ ሌሎች ሕይወት አድን አገልግሎቶች ተቀናጅተው መቅረባቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።

በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ 22 ዞኖች ውስጥ ለተጨማሪ መከላከያ ይረዳ ዘንድ ሁለት ዓይነት የፖሊዮ ክትባቶች በጋራ መሰጠታቸው ተጠቁሟል፡፡

የክትባት ዘመቻው በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት መሪነት ከዓለም ጤና ድርጅት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ከታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0