በቀጣናዊ የኢነርጂ ንግድ ላይ ትኩረት ያደረገው 27ኛው የአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ፎረም በሶማሊያ ተካሄደ
15:16 29.01.2026 (የተሻሻለ: 15:24 29.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በቀጣናዊ የኢነርጂ ንግድ ላይ ትኩረት ያደረገው 27ኛው የአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ፎረም በሶማሊያ ተካሄደ
ውይይቱ ቀጣናዊ የኢነርጂ ንግድን በማስፋፋት፣ ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ፕሮጀክቶችን በማሻሻል እና ለቤተሰቦችና ለንግድ ተቋማት ተመጣጣኝ የኃይል አቅርቦት ማቅረብ ላይ ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በሶማሊያ የፋይናንስ ሚኒስትር ቢሂ ኢማን ሲጌ ሰብሳቢነት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን የፋይናንስ ሚኒስትሮች በአካል የተገኙ ሲሆን፣ የኬንያ እና የሱዳን ተወካዮች ደግሞ በበይነ-መረብ ተሳትፈዋል።
“ፎረሙ ለኢነርጂ መሠረተ ልማት ግንባታ የሚሆን ፋይናንስን ማሰባሰብ በሚቻልባቸው ተግባራዊ መፍትሄዎች ላይ መክሯል” ሲሉ የሶማሊያ ፋይናንስ ሚኒስትር ቢሂ ኢማን ሲጌ ተናግረዋል፡፡
ዝቅተኛ ዋጋ ያለው እና አስተማማኝ የኢነርጂ አቅርቦት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለቀጣናው መረጋጋት ወሳኝ መሆኑ በስብሰባው ላይ በስፋት ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X