ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የሶሪያ አቻቸው አሕመድ አል-ሻራ በሩሲያ የጦር ሰፈር ጉዳይ ላይ መወያየታቸው ተገለፀ
14:59 29.01.2026 (የተሻሻለ: 15:04 29.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የሶሪያ አቻቸው አሕመድ አል-ሻራ በሩሲያ የጦር ሰፈር ጉዳይ ላይ መወያየታቸው ተገለፀ
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰጡት ተጨማሪ መግለጫዎች፦
🟠 በአቡ ዳቢ የሚካሄደው የዩክሬን ጉዳይ ውይይት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለሁለት ቀናት ሊቆይ ይችላል።
🟠 የውይይቱ ዝርዝር ሁኔታዎች እስከ እሁድ ድረስ ስምምነት ይደረግባቸዋል፤ ሆኖም ይህ በጉዳዩ ፍሬ ነገር ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም።
🟠 ክሬምሊን የ"ኒው ስታርት" የስትራቴጂካዊ የጦር መሣሪያዎች ቅነሳ ስምምነትን ለማራዘም ላቀረበው ጥያቄ ከአሜሪካ ምላሽ እየጠበቀ ይገኛል።
🟠 የ"ኒው ስታርት" ስምምነትን የሚተካ አዲስ ስትራቴጂካዊ የመረጋጋት ስምምነት ማርቀቅ፣ በርካታ ሁኔታዎችን ያካተተ ረጅም እና ውስብስብ ሂደት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X