ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ85 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
13:56 29.01.2026 (የተሻሻለ: 14:04 29.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ85 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
በዚህም የእቅዱን 81 በመቶ ማሳካቱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ የ2018 በጀት ግማሽ ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልጸዋል፡፡
የደንበኞቹ ቁጥር 87.1 ሚሊዮን መድረሱን መናገራቸውንም የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግባለች፡፡
በዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
በቴሌብር 1.94 ትሪሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተካሂዷል።
የግብይት መጠን 1 ቢሊዮን ደርሷል።
የቴሌብር ደንበኞች ቁጥር 58.61 ሚሊዮን ተሻግሯል።
1.6 ሚሊዮን ዶላር በቴሌብር አማካኝነት ሬሚታንስ አስገኝቷል።
4.2 ሚሊዮን ደንበኞች 8.6 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አግኝተዋል።
5 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ 33 ቢሊዮን ብር ቆጥበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia