የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.01.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ

በሀገሪቱ የፋይናንስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አውቶሜትድ ሥርዓት የሚካሄደው ግብይቱ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መድረክ ላይ ሁሉም ንግድ ባንኮች ስለ ገበያው እኩል መረጃ ኖሯቸው የሚከናወን መሆኑን ብሔራዊ ባንክ በይፋዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ “ለተሳታፊ ሁሉ ግልጽ፣ ፈጣንና በመመሪያ የተመራ የገበያ አካባቢ ይፈጥራል። መድረኩ የገበያ ዲሲፕሊንን ለማጠንከር፣ የዋጋ ሂደትን ለማሻሻልና የፋይናንስ ገበያ ሪፎርምን ለመደገፍ ትልቅ ግብዓት ነው።” ሲሉ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡

የገበያው አሠራር በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የሚመራ ሲሆን፣ ሁሉም ተሳታፊ ባንኮች የተቀመጡ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እና የውጭ ምንዛሬ ተጋላጭነት ገደቦችን የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ገበያ ከዓለም አቀፍ አሠራሮች ጋር ለማጣጣም እና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ይበልጥ ዘመናዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል ዘመናዊ የግብይት አውታር አስጀመረ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0