በሶማሊያ ምክር ቤት አንድ ሚኒስትር ከፓርላማ አባል ጋር ቡጢ ገጠሙ
17:40 28.01.2026 (የተሻሻለ: 17:44 28.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሶማሊያ ምክር ቤት አንድ ሚኒስትር ከፓርላማ አባል ጋር ቡጢ ገጠሙ
የሶማሊያ ፓርላማ የ2012ቱን የሽግግር ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል ውይይት ሊጀምር ቀጠሮ ይዞነበር፡፡ ሆኖም በስብሰባው ወቅት የተቃዋሚ ፓርላማ አባላት ከመቀመጫቸው በመነሳት መዝሙር በመዘመር እና መፈክሮችን በጩኸት በማሰማት መርሃ ግብሩን ለማስተጓጎል መሞከራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር አብዱላሂ ሼክ ኢስማኢል ፋርታግ ከፓርላማ አባቱ ሀሰን ፊሪንቢ ጋር ቡጢ ሲለዋወጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል።
በሕገ-መንግሥቱ ላይ እንዲደረጉ የታቀዱት ዋና ዋና ማሻሻያዎች፤ ሀገሪቱ "አንድ ሰው - አንድ ድምፅ" ወደሚለው ቀጥተኛ የምርጫ ሥርዓት እንድትሸጋገር እና የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን ለማጠናከር ያለሙ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X