የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 40 ሚሊዮን የቡና ችግኞችን ሊተክል መሆኑን ገልፀ
15:55 28.01.2026 (የተሻሻለ: 16:04 28.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 40 ሚሊዮን የቡና ችግኞችን ሊተክል መሆኑን ገልፀ
ችግኞቹ በሚያዝያ ወር የሚተከሉና ለክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ጥቅም ላይ እንዲውሉ መዘጋጀታቸውን የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን አስታውቋል።
በማኅበረሰብ ንቅናቄ አዲስና በእድሳት ችግኞችን ለመትከል፡-
ከ17 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የጉድጓድ ቁፋሮ እየተከናወነ ነው፡፡
ከ1.4 ሚሊዮን ቶን በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
በክልሉ ቡናን በኩታ ገጠም በዘመናዊ መንገድ የማልማት ልማድ እየሰፋ መምጣቱን ተከትሎ የሚገኘው የቡና ምርት በአማካይ ወደ 9 ኩንታል ማደጉንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን ከ235ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና መሸፈኑ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X