የገንዘብ ኖትን በሀገር ውስጥ ማተም ግትልትል ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ እርምጃ ነው - ባለሙያ
20:05 27.01.2026 (የተሻሻለ: 20:14 27.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የገንዘብ ኖትን በሀገር ውስጥ ማተም ግትልትል ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ እርምጃ ነው - ባለሙያ
የገንዘብ ኖትን በሌላ ሀገር ማሳተም ሀገርን ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እና ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት እንደሚዳርግ የፕራግማ ካፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ገንዘብ በውጭ ሀገር ሲታተም ለባንኮች የገንዘብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት ይቸግራል። ምክንያቱም ብሔራዊ ባንክ የገበያውን ፍላጎት እና የገንዘብ ሥርጭቱን ማስማማት አለበት። በዚህም የውጭ አታሚዎች ገንዘቡን አትመው ሀገር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ባንኮቹ ለመጠበቅ ይገደዳሉ" ብለዋል።
ገንዘብን በሀገር ውስጥ ማተም የቁጥጥር እና ሎጂስቲክ ውስብስብ ሂደቶችን እንደሚቀርፍም አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የገንዘብ ኖትን በተለያዩ ሀገራት ማሳተም ያለውን አደጋ ለማስቀረት፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ የገንዘብ ኖትን በሀገር ውስጥ የማተም አቅም እየገነባ እንደሚገኝ፤ "የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ በቅርቡ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X