የዙሉ ንጉሥ ክዋዙሉ-ናታል ከሚለው የግዛት ሥያሜ 'ናታል' የሚለውን የፖርቹጋል ቃል በመሰረዝ መጠሪያው እንዲቀየር ሀሳብ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዙሉ ንጉሥ ክዋዙሉ-ናታል ከሚለው የግዛት ሥያሜ 'ናታል' የሚለውን የፖርቹጋል ቃል በመሰረዝ መጠሪያው እንዲቀየር ሀሳብ አቀረቡ
የዙሉ ንጉሥ ክዋዙሉ-ናታል ከሚለው የግዛት ሥያሜ 'ናታል' የሚለውን የፖርቹጋል ቃል በመሰረዝ መጠሪያው እንዲቀየር ሀሳብ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.01.2026
ሰብስክራይብ

የዙሉ ንጉሥ ክዋዙሉ-ናታል ከሚለው የግዛት ሥያሜ 'ናታል' የሚለውን የፖርቹጋል ቃል በመሰረዝ መጠሪያው እንዲቀየር ሀሳብ አቀረቡ

የደቡብ አፍሪካ ትልቁ ብሔረሰብ ባሕላዊ መሪ የሆኑት ሚሱዙሉ ካዝዌሊቲኒ፤ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት የኢሳንድልዋና ጦርነት መታሰቢያ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። "ናታል" የሚለው የቃሉ ክፍል መነሻው የቅኝ ግዛት በመሆኑ ሥያሜው እንዲሰረዝ ዘመቻ እንደሚጀምሩ ገልጸዋል።

ይህ የአውሮፓውያን ሥያሜ እ.ኤ.አ 1497 ፖርቹጋላዊው አሳሽ ቫስኮ ዳ ጋማ አሁን ደርባን ወደብ ተብሎ የሚጠራውን ቦታ በአፍ መፍቻ ቋንቋው "ናቲቪቲ" (ልደት) በማለት ከሠየመው በኋላ የመጣ ነው።

በኋላም አውሮፓውያን ሰፋሪዎች እ.ኤ.አ በ1839 "የናታሊያ ሪፐብሊክን" ሲመሠርቱ የቃሉን መነሻ ተጠቅመውበታል። ይህ ሪፐብሊክ በኋላ ወደ የናታል ቅኝ ግዛት፤ ከዚያም ወደ "ናታል ጠቅላይ ግዛት" ተቀይሯል።

"ክዋዙሉ" ማለት "የዙሉዎች ምድር" ማለት ሲሆን እ.ኤ.አ በ1816 በንጉሥ ሻካ የተመሠረተውን ታሪካዊ የዙሉ መንግሥት ያመለክታል። ይህ ቃል በአፓርታይድ ዘመን በከፊል ራሱን የቻለ የዙሉ "ባንቱስታን" ግዛት ስም ሆኖ መጠቀሙ ይታወሳል። በደቡብ አፍሪካ ከፋፋዩ የዘር ሥርዓት ካበቃ በኋላ የአውሮፓውያን እና የአፍሪካውያንን የአሠያየም ባሕል ለማዋሃድ የናታል ጠቅላይ ግዛት ከክዋዙሉ ጋር ተቀላቅሎ "ክዋዙሉ-ናታል" የሚለውን ሥም ይዟል።

የዙሉ ንጉሥ ቃል አቀባይ፤ ልዑል ቱላኒ ዙሉ የንጉሡን የሥም ለውጥ ጥሪ በመደገፍ፤ የአውራጃው አብዛኛው ሕዝብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ዙሉ መሆኑን በመጥቀስ የክልሉ ሥም ወደ ዙሉ ቋንቋ መለወጥ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0