ባለፉት ስድስት ወራት የ237 ኪሎሜትር የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለፀ
17:52 27.01.2026 (የተሻሻለ: 18:04 27.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባለፉት ስድስት ወራት የ237 ኪሎሜትር የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለፀ
በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የ133 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችን ማጠናከርና ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም የ6577 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ የጥገና ሥራዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታውቋል፡፡
የኢተያ- አርሲ ሮቤ፣ እስቴ-ማዳ፣ የድሬዳዋ ሽንሌ እና የድሬዳዋ-ቃቆ መንገድ ፕሮጀክቶች ዋና ዋና ሥራዎች በግማሽ ዓመቱ እንደተጠነቀቁ ተቋሙ ገልጿል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻም ከ16 ሺህ 976 ኪሎሜትር በላይ የሚሸፍኑ የመንገድ ግንባታ እና ልዩ ልዩ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ግብ ተቀምጦ እየተሠራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ተቋሙ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችን ከአስፋልት ጋር በማዋሀድ ለመንገድ ንጣፍ በመጠቀም የአገልግሎት ጊዜን ለማራዘም እና ለጥገና የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት በተሞክሮነት ማቅረቡን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X