ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶችን በባቡር የማጓጓዝ ሙከራ ዛሬ ትጀምራለች ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶችን በባቡር የማጓጓዝ ሙከራ ዛሬ ትጀምራለች ተባለ
ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶችን በባቡር የማጓጓዝ ሙከራ ዛሬ ትጀምራለች ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶችን በባቡር የማጓጓዝ ሙከራ ዛሬ ትጀምራለች ተባለ

ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ደቡባዊ ዳርቻ ከሚገኘው የንዶዴ የባቡር ዴፖ በሚጀመረው የሙከራ ሂደት፤ 120 ሺህ ሊትር ናፍጣ እንደሚጓጓዝ ተሰምቷል።

ዳራ፦ የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በቦቴ የሚገባው ነዳጅ ከያዝነው ዓመት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በባቡር እንደሚጓጓዝ አስታውቆ ነበር፡፡

ዕቅድ፦ በቀን እስከ አስር ጊዜ በባቡር በመመላለስ በዓመት 4.2 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ለማጓጓዝ እንደታቀደ ተገልጿል፡፡ እዚህ ላይ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር በሰዓት 37 ኪ.ሜ የነበረውን የጉዞ ፍጥነት ወደ 60 ኪ.ሜ እንዳሳደገ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡

የሚጠበቀው ውጤት

የነዳጅ አቅርቦት ችግርን መቅረፍ፣

የነዳጅ ማጓጓዣ ጊዜን መቀነስ፣

የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ ቅናሽ ማምጣት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በጅቡቲ ዶራሌ የሚገኘውን የሆራይዘን ተርሚናል በጎበኙበት ወቅት፤ ነዳጅ በአስቸኳይ በባቡር መስመር እንዲጓጓዝ መመሪያ መስጠታቸው ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0