አሜሪካ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ወታደራዊ ግጭት በምድር፣ በአየር እና በባሕር ኃይል እየተዘጋጀች ነው - የሊባኖስ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ወታደራዊ ግጭት በምድር፣ በአየር እና በባሕር ኃይል እየተዘጋጀች ነው - የሊባኖስ ባለሙያ
አሜሪካ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ወታደራዊ ግጭት በምድር፣ በአየር እና በባሕር ኃይል እየተዘጋጀች ነው - የሊባኖስ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.01.2026
ሰብስክራይብ

አሜሪካ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ወታደራዊ ግጭት በምድር፣ በአየር እና በባሕር ኃይል እየተዘጋጀች ነው - የሊባኖስ ባለሙያ

የዩናይትድ ሰቴትስ ወታደራዊ ዝግጅት አሜሪካ እና እስራኤል ኢራንን ወደ መምታት አፋፍ አድርሷቸዋል ሲሉ ብሪጋዴር ጄኔራል ማሊክ አዩብ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ትራምፕ እና ኔታንያሁ "ለኢራን ችግር ቀጣዩን የመፍትሄ ምዕራፍ ነድፈዋል" ያሉት ጄኔራሉ፤ በኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጁነት ምክንያት "ድንገተኛ ጥቃት" የማድረስ ዕድሉ አምልጧል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ወታደራዊ ባለሙያው እንደሚያምኑት፤ ትራምፕ የኢራንን አለመረጋጋት በማበረታታቸው ስህተት ሰርተዋል። ይህም የኢራን የደህንነት ተቋማት አስቀድመው በመቶዎች የሚቆጠሩ መረቦችን እንዲበጣጥሱ ዕድል ሰጥቷል ብለዋል፡፡

እስራኤል ከዚህ ቀደም ከቴህራን ጋር በገባችበት ፍጥጫ መቋቋም አለመቻሏን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከኢራን ጋር በሚደረግ ጦርነት ውስጥ መሳተፍ "ከባድ ስህተት" እንደሚሆንባት ተናግረዋል።

ጦርነት ቢነሳ ኢራን አሜሪካ ላይ ኃይል ለመያዝ ስትል እስራኤልን ልትመታ ትችላለች ያሉት አዩብ፤ እስራኤል በጦርነቱ ከተሳተፈች የሚከተለው መዘዝ አስከፊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።

በቀጣናው የሚኖረውን ተፅዕኖ በተመለከተ፤ ግጭት ከተቀሰቀሰ የዓረብም ሆነ የኢራን የነዳጅ አቅርቦቶች ለአደጋ ስለሚጋለጡ፤ እንደ ሳዑዲ አረቢያ ያሉ የባሕረ ሰላጤው ሀገራትን ፍላጎት እንደማያገለግል አዩብ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በወሳኙ የሆርሙዝ የባሕር በር የመርከብ ጉዞ ደህንነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባና መስመሩ ቢዘጋ 20 በመቶ የዓረብ ነዳጅ እና 30 በመቶ የዓለም አቀፍ ንግድ እንደሚቋረጥ ገልፀዋል።

"ይህ የባሕር በር ቢዘጋ ትልቁ ተሸናፊ ቻይና ትሆናለች፤ ለዚህም ነው ራዳሮችን እና የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ጨምሮ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ለኢራን የምታቀርበው" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0