የምዕራባውያን ባለሙያዎች የሩሲያን 'ኦሬሽኒክ' ሚሳኤል ሥርዓት መመከት እንደማይቻል አምነዋል - የሩሲያ የውጭ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ
19:51 26.01.2026 (የተሻሻለ: 19:54 26.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የምዕራባውያን ባለሙያዎች የሩሲያን 'ኦሬሽኒክ' ሚሳኤል ሥርዓት መመከት እንደማይቻል አምነዋል - የሩሲያ የውጭ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ
የምዕራባውያን ባለሙያዎች የሩሲያን 'ኦሬሽኒክ' ባሊስቲክ ሚሳኤል ሥርዓት ለመመከት የሚያስችል ወታደራዊም ሆነ ቴክኒካዊ አቅም እንደሌላቸው ማመናቸውን የሩሲያ የውጭ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር ሰርጌ ናሪሽኪን ገልፀዋል።
“ባለሙያዎችም ሆኑ ወታደራዊ ስፔሻሊስቶች እነዚህን ሥርዓቶች ለመመከት የሚያስችል ቴክኒካዊም ሆነ ወታደራዊ-ቴክኒካዊ መሣሪያዎች እንደሌሏቸው አምነዋል” ሲሉ ናሪሽኪን አክለው ተናግረዋል።
የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ፤ በዩክሬን ልቮቭ ክልል በሚገኝ ወታደራዊ ተቋም ላይ የተፈጸመውን የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ጥቃት ተከትሎ በምዕራባውያን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ክበቦች ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ እንደታየ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የሩሲያ ጦር ኃይል ጥር 1 ቀን ተንቀሳቃሽ የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሥርዓትን በመጠቀም በልቮቭ ክልል የአውሮፕላን ጥገና ፋብሪካን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቀደም ሲል አስታውቋል።
ፋብሪካው ምዕራባውያን ለዩክሬን የሰጧቸውን የኤፍ-16 እና ሚግ-29 ተዋጊ ጄቶች ለመጠገን እንደሚያገለግል እንዲሁም በሩሲያ ሲቪል ተቋማት ላይ ጥቃት የሚሰንዝሩ ሰው አልባ ድሮኖችን ያመርት እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X