የብሪክስ ዲጂታል ገንዘቦች የአሜሪካን የፋይናንስ የበላይነት በመስበር አፍሪካን ያጠናክራሉ - የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ አባል

ሰብስክራይብ

የብሪክስ ዲጂታል ገንዘቦች የአሜሪካን የፋይናንስ የበላይነት በመስበር አፍሪካን ያጠናክራሉ - የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ አባል

ሕንድ የብሪክስ አባል ሀገራትን በዲጂታል ገንዘብ ለማስተሳሰር ያቀረበችው ሀሳብ፤ በዓለም አቀፍ ፋይናንስ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣና የአሜሪካን የበላይነት የሚያዳክም መሆኑን አንዲሌ ንግክሲታማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

“ይህ የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ማብቂያ ጅማሮ ነው” ያሉት ንግክሲታማ፤ ብሪክስ እና ሌሎች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አማራጭ የገንዘብ ልውውጥ ሥርዓቶችን ከተገበሩ ከዶላር በመላቀቅ “የአሜሪካ የበላይነት እንዲያበቃ” ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል።

የዲጂታል ገንዘብ ውህደት ለደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ የገለጹት የሕዝብ እንደራሴው፤ ይህም ፍትሕዊ የንግድ ውል፣ ዝቅተኛ የቱሪስት ወጪ እና ለማዕድን ወጪ ንግድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።

ከዶላር ውጪ ግብይት መፈጸም የደቡብ አፍሪካን ገንዘብ (ራንድ) ለማጠናከር እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ለማስፈን እንደሚረዳም ጠቁመዋል።

ለአፍሪካ ከዶላር ጥገኝነት መውጣት የሀገራቱን የመደራደር አቅም የሚያሻሽል እና አኅጉራዊ ውህደትን የሚያፋጥን ነው ሲሉም ንግክሲታማ ገልፀዋል።

ሀገራት “ይበልጥ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ” እንዲገበያዩ እና “የኳሜ ንክሩማህ የተባበረች አፍሪካ ህልም” ዳግም እንዲያንሰራራ በማድረግ፤ አኅጉሪቱ እንደ አንድ ጠንካራ የኢኮኖሚ ኃይል እንድትሰለፍ ይረዳታል።

አክለውም የዶላርን የበላይነት ከፖለቲካዊ ጫና እና ማዕቀብ ጋር አያይዘውታል። አሜሪካ ሌሎች ሀገራትን ለመቆጣጠር ከወታደራዊ ኃይሏ በተጨማሪ “ኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነትን” እንደምትጠቀም ገልጸው፤ የዶላርን ማዕከላዊ ሚና ማስቀረት ይህን ተፅዕኖ በማዳከም ለደቡባዊው ዓለም ከፍተኛ ሉዓላዊነት ያጎናጽፋል ብለዋል።

አማራጭ የገንዘብ ሥርዓት የአፍሪካ ሀገራት በጠንካራ አቋም እንዲደራደሩ፣ የመሬት ማሻሻያዎችን እንዲደግፉ እና ዘላቂ መረጋጋትን እንዲያሰፍኑ እንደሚረዳቸው ንግክሲታማ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በዶላር ላይ ያለው ጥገኝነት ከተሰበረ፤ “ለደቡባዊው የዓለም ክፍል የነፃነት ቀን ነው” ሲሉም ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0