የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ
18:16 26.01.2026 (የተሻሻለ: 18:24 26.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ
10ኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ዉድድር “ስፖርት፣ ብዝሃነትና እውቀት ለልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ ከጥር 17 እስከ የካቲት 1 2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡
የዘንድሮው ውድድር፦
49 ዩኒቨርሲቲዎች፣
15 የስፖርት ዓይነቶች፣
ከ4500 መቶ በላይ ተወዳዳሪዎችን ያሳትፋል፡፡
ውድድሩን ለማሰናዳት ከመቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ጀማል አባፊጣን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
የስፖርት ፌስቲቫሉ ከ2017 በፊት በነበሩት ሰባት ዓመታት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት መካሄዱ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia