ኡጋንዳ ከ19 ዓመታት ቆይታ በኋላ ጦሯን ከሶማሊያ እንደምታስወጣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኡጋንዳ ከ19 ዓመታት ቆይታ በኋላ ጦሯን ከሶማሊያ እንደምታስወጣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ አስታወቁ
ኡጋንዳ ከ19 ዓመታት ቆይታ በኋላ ጦሯን ከሶማሊያ እንደምታስወጣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.01.2026
ሰብስክራይብ

ኡጋንዳ ከ19 ዓመታት ቆይታ በኋላ ጦሯን ከሶማሊያ እንደምታስወጣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ አስታወቁ

ኡጋንዳ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ጦሯን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከሶማሊያ ለማስወጣት ማቀዷን የኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ገልጸዋል።

ጄኔራል ካይኔሩጋባ፤ እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ በአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ስር ሶማሊያ የሚገኘው የኡጋንዳ ጦር ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ባለፈው ሐምሌ ወር ጥሪ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ አዛዡ በወቅቱ አሜሪካ ከአል-ሸባብ* ቡድን ተወካዮች ጋር በምስጢር ድርድር እያደረገች ነው የሚል ክስ አቅርበዋል።

ℹ በታኅሣሥ 2024 የተጠናቀቀውን የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) የተካው "የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና የመረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ" (አውሶም) 11 ሺ ወታደሮች ያሉት ሲሆን ስብጥሩም የሚከተለው ነው፦

4,500 ከኡጋንዳ፣

2,500 ከኢትዮጵያ፣

1,500 ከጅቡቲ፣

1,400 ከኬንያ፣

1,100 ከግብፅ፡፡

*አል-ሸባብ ለአል-ቃይዳ የሽብር ቡድን ታማኝነቱን የገለጸ፤ ሩሲያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ውስጥ የታገደ ድርጅት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0