ኢትዮጵያ የዓለም ወታደራዊ ኃይል ደረጃዋን አሻሻለች

ኢትዮጵያ የዓለም ወታደራዊ ኃይል ደረጃዋን አሻሻለች
በግሎባል ፋየር ፓወር የ2026 ወታደራዊ ኃይል ደረጃ መሠረት ኢትዮጵያ፤ በ0.8525 የኃይል መለኪያ በ2025 ከነበረችበት 52ኛ ደረጃ 5 ደረጃዎችን አሻሽላ 47 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከአፍሪካ ባለችበት 5ኛ ደረጃ ቀጥላለች፡፡
በ2026 ግብፅ ከአፍሪካ ቀዳሚ ወታደራዊ ኃያልነቷን ያረጋገጠች ሲሆን በ0.3651 የኃይል መለኪያ ከአፍሪካ 1ኛ፤ ከ145 ሀገራት መካከል ደግሞ ከዓለም 19ኛ ደረጃን ይዛለች።
አልጄሪያ በአህጉሪቱ 2ኛ (በዓለም 27ኛ) ደረጃን ስትይዝ፤ ተከታዮቹ ሀገራት፦
ናይጄሪያ (በዓለም 33ኛ)
ደቡብ አፍሪካ (40ኛ)
ኢትዮጵያ (47ኛ)
ሞሮኮ (56ኛ)
አንጎላ (59ኛ)
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (64ኛ)
ሱዳን (66ኛ)
ቱኒዝያ (79ኛ)፤ ከአፍሪካ 10 ወታደራዊ ኃይሎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ሱዳን እና ቱኒዝያን ጨምሮ 14 የአፍሪካ ሀገራት በዓለም የወታደራዊ ኃይል ዝርዝር ውስጥ የደረጃ መሻሻል አሳይተዋል። ከአፍሪካ ሀገራት 17ቱ ደረጃቸው ሲቀንስ የ7ቱ ደግሞ እንደነበረ ቀጥሏል።
የግሎባል ፋየር ፓወር የኃይል መለኪያ፤ የወታደር ቁጥር፣ የጦር መሣሪያዎች፣ በጀት፣ ሎጅስቲክስ፣ የተፈጥሮ ሀብቶች እና ጂኦግራፊን ጨምሮ ከ60 በላይ አመላካቾችን በመጠቀም ይሰላል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X