በአማራ ክልል የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ተከትሎ ከተነቃቃው የቱሪዝም ዘርፍ ከ7.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
16:05 26.01.2026 (የተሻሻለ: 16:14 26.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ተከትሎ ከተነቃቃው የቱሪዝም ዘርፍ ከ7.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
ገቢው በጥምቀት በዓል የተገኘውን ሳያካትት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ከቱሪዝም ዘርፉ የተሰበሰበ እንደሆነ የክልሉ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
በግማሽ ዓመቱ 24 ሺህ የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች የክልሉን ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች መጎበኝታቸውን የቢሮው ኃላፊ መልካሙ ፀጋዬ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የሰላም ግንባታና የልማት ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፉ ማገገም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
“ያለ ሰላም ቱሪዝም ሊታሰብ አይችልም፤ በቅርቡ የታየው የጸጥታ መሻሻል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ክልሉ ታዋቂ የቱሪስት መዳረሻዎች በድፍረት እንዲመለሱ በር ከፍቷል” ብለዋል።
እንደ ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እና የፋሲል ግንብ ያሉ መዳረሻዎች ተጠግነውና ተጠብቀው ለጎብኚዎች ዝግጁ መደረጋቸው የጎብኚዎች አማካይ የቆይታ ጊዜ ቀደም ሲል ከነበረበት ከሁለት እስከ ሦስት ቀናት ወደ አምስት ቀናት ከፍ እንዲል ማድረጉንም ገልፀዋል።
ክልሉ ይህን መነቃቃት በዘላቂነት ለማስቀጠል የ25 ዓመት የቱሪዝም ልማት ዕቅድ እና የ5 ዓመት ስትራቴጂዊ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን ቢሮው ይፋ አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

