ኢትዮጵያ ባሕር ኃይሏን በሥልጠና ለማጠናከር ከደቡብ አፍሪካ እና ሩሲያ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ደረሰች
15:34 26.01.2026 (የተሻሻለ: 15:44 26.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባሕር ኃይሏን በሥልጠና ለማጠናከር ከደቡብ አፍሪካ እና ሩሲያ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ደረሰች
በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ በነበረው የብሪክስ ሀገራት ዊል ፎር ፒስ (Will For Peace 2026) የባሕር ልምምድ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልዑካን ቡድን ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡
ኢትዮጵያ በልምምዱ በቀጣይ ከብሪክስ ሀገራት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚጠቅሙ ግብዓቶች እንዳገኘችበት የልዑካን ቡድኑ መሪ ምክትል አድሚራል ክንዱ ገዙ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ ከልምምዱ ጎን ለጎን ከደቡብ አፍሪካ ባሕር ኃይል አቻቸውና ከሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንዳደረጉ እና የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል በተለያዩ የሥልጠና ዘርፎች ለመደገፍ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia