የወርቅ እና የብር ምርቶች ዋጋ የምንግዜም ከፍተኛው ሆኖ ተመዘገበ
10:34 26.01.2026 (የተሻሻለ: 10:44 26.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የወርቅ እና የብር ምርቶች ዋጋ የምንግዜም ከፍተኛው ሆኖ ተመዘገበ
ዛሬ ሰኞ ማለዳ የወርቅ እና የብር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቀጥሏል፡፡ እንደ ንግድ መረጃዎች መሠረት፤ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ ከ5,100 ዶላር በላይ እንዲሁም የአንድ ወቄት ብር ዋጋ ከ109 ዶላር በላይ በመሆን አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል።
በኢትዮጵያ መደበኛ ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 1:06 ላይ በኒውዮርክ ኮሜክስ ገበያ የሚያዝያ ወር የወርቅ የወደፊት ግብይት ካለፈው መዝጊያ ጋር ሲነጻጸር በ1.82 በመቶ ወይም በ91.30 ዶላር ጭማሪ አሳይቶ በአንድ ወቄት 5,109.71 ዶላር እየተገበያየ ነበር። ቀደም ሲል በዕለቱ የንግድ ክፍለ ጊዜ ዋጋው እስከ 5,128.85 ዶላር ደርሶ ነበር።
በተመሳሳይ የመጋቢት የብር የወደፊት ግብይት በ6.49 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአሁኑ ወቅት በአንድ ወቄት 107.92 ዶላር እየተገበያየ ሲሆን ቀደም ብሎም እስከ 109.32 ዶላር በመድረስ አዲስ ከፍተኛ ዋጋ አስመዝግቧል።
ፕላቲነም በበኩሉ በአንድ ወቄት 2,897 ዶላር በመሆን የምንግዜም ከፍተኛ ዋጋው ላይ ደርሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X