የምዕራባውያን 'ትብብር' ብዙ ጊዜ የአፍሪካን ሉዓላዊ የልማት ዕድል ያደናቅፋል - ደቡብ አፍሪካዊ ተንታኝ
የምዕራባውያን 'ትብብር' ብዙ ጊዜ የአፍሪካን ሉዓላዊ የልማት ዕድል ያደናቅፋል - ደቡብ አፍሪካዊ ተንታኝ
የምዕራባውያን የኢኮኖሚ እና የፖሊሲ ጫናዎች በዓለም አቀፍ ትብብር ስም በደቡባዊው የዓለም ክፍል ያሉትን ሀገራዊ ዕድገቶች በተደጋጋሚ ይገድባሉ ሲሉ በኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ዛኬሌ ንድሎቩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ተንታኙ ያቀረቧቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 በምዕራባውያን የፖሊሲ ገደቦች ላይ፦ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ ያሉ ተቋማት በማደግ ላይ ባሉ የደቡብ ዓለም ሀገራት ላይ ፖሊሲዎችን "ይጭናሉ"። ለዚህም ቀደም ሲል የነበሩ የመዋቅራዊ ማስተካከያ ፕሮግራሞችን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
🟠 ስለ ሉዓላዊ ልማት፦ ንድሎቩ እውነተኛ ሉዓላዊ ልማት፤ "አንዲት ሀገር ያለ ምንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ራሷን የማልማት አቅም" ማለት እንደሆነ ገልጸዋል።
🟠 ስለ መሬት ይዞታ ማሻሻያ፦ በዚምባብዌ እና በደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን የመሬት ክፍፍል ምዕራባውያን የሚቃወሙት፤ ታሪካዊ ፍትሕን በመመከት "ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማስቀጠል" እና የአውሮፓ ዝርያ ያላቸውን ጥቂት ነዋሪዎች ጥቅም ለመጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።
🟠 ስለ ዘላቂ አደጋዎች፦ የምዕራባውያንን መመሪያ መከተል "ሙሉ በሙሉ ነፃ የመሆን አቅምን ያዘገያል" ሲሉ ደምድመዋል። በመሆኑም የአፍሪካ ሀገራት ይህንን ጫና በጋራ እንዲመክቱ አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X