ባለ ከፍተኛ ቁጥር ተከታዩ የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪ ካቢ ላሜ በ900 ሚሊዮን ዶላር የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የንግድ ስምምነት ፈረመ
18:58 25.01.2026 (የተሻሻለ: 19:04 25.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ባለ ከፍተኛ ቁጥር ተከታዩ የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪ ካቢ ላሜ በ900 ሚሊዮን ዶላር የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የንግድ ስምምነት ፈረመ
ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቢ ላሜ ከማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ወደ ከፍተኛ ባለአክሲዮንነት የተሸጋገረበትን የ900 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ መድረሱን የኩባንያውን ከፊል ድርሻ የገዛው የአሜሪካው "ሪች ስፓርክል ሆልዲንግስ" አስታውቋል።
በስምምነቱ መሠረት ሪች ስፓርክል ለሚቀጥሉት 36 ወራት የላሜን የንግድ ስም ሽርክናዎች እና የኢ-ኮሜርስ ሥራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የመምራት ብቸኛ መብት ማግኘቱን ገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዝ የካቢ ላሜን "ዲጂታል መንታ" መፍጠር የስምምነቱ ቁልፍ አካል ነው። ይህ ቴክኖሎጂ የካቢ ላሜን ምናባዊ ምሥል በመጠቀም በተለያዩ ቋንቋዎች በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን የቀጥታ ስርጭት እና በብዙ ቋንቋዎች ይዘቶችን ማቅረብ የሚችል መሆኑ ተገልጿል።
ሽርክናው የላሜን 360 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተከታዮች ከዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ ሽያጭ ጋር በማገናኘት በዓመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ ለማስመዝገብ ያለመ ነው። ሥራውም በመጀመሪያ በአሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ ይጀምራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X