ሱዳን ከአማፂው የፈጥሮ ደራሽ ኃይል ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ 122 የውጭ ቅጥረኞችን ለፍርድ እንዳቀረበች እና ህጻናት ወታደሮችን መታደጓን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሱዳን ከአማፂው የፈጥሮ ደራሽ ኃይል ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ 122 የውጭ ቅጥረኞችን ለፍርድ እንዳቀረበች እና ህጻናት ወታደሮችን መታደጓን አስታወቀች
ሱዳን ከአማፂው የፈጥሮ ደራሽ ኃይል ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ 122 የውጭ ቅጥረኞችን ለፍርድ እንዳቀረበች እና ህጻናት ወታደሮችን መታደጓን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.01.2026
ሰብስክራይብ

ሱዳን ከአማፂው የፈጥሮ ደራሽ ኃይል ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ 122 የውጭ ቅጥረኞችን ለፍርድ እንዳቀረበች እና ህጻናት ወታደሮችን መታደጓን አስታወቀች

የሱዳን የሕግ አካላት በፈጥሮ ደራሽ ኃይሉ ተመልምለው በሚዋጉ የውጭ ሀገር ቅጥረኞች ላይ የወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው እና አንዳንዶቹ ከወዲሁ ሞት ፍርድ እንደተቀጡ ገልጸዋል። በተጨማሪም 135 በግዳጅ ተመልምለው የነበሩ ህጻናት ወታደሮች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ባለሥልጣናቱ አማፂ ቡድኑ ወታደሮችን በዋነኝነት ከቻድ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኢትዮጵያ እና ከኮሎምቢያ እንደሚመልምል በመጥቀስ ከሰዋል።

በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ኮሚቴ ያወጣቸው ዋና ዋና ግኝቶች፦

🟠 እ.ኤ.አ በሚያዚያ 2023 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቢያንስ 188,405 የወንጀል መዝገቦች ተመዝግበዋል።

🟠 የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድርጊቱን ከዚህ ቀደም ብታስተባብልም ለአማፂያኑ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የሚያሳዩ የኤግዚቢት ማስረጃዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

🟠 በፈጣኖ ደራሽ ኃይሉ በታዳጊዎች ላይ ጭምር የሚፈጸም ስልታዊ የጾታ ጥቃት መኖሩ ተመልክቷል።

🟠 በኤል ጄኔና በማሳሊት ጎሳ ላይ የተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን እና በካዱግሊ መዋዕለ ሕፃናት ላይ በደረሰ የከባድ መሣሪያ ጥቃት 114 ሰዎች፤ አብዛኞቹ ሴቶችና ሕጻናት የተገደሉበትን የጅምላ ጭፍጨፋ ኮሚቴው አረጋግጧል።

በተያያዘ ዜና፤ በፖርት ሱዳን የሚገኘው የጸረ-ሽብር ፍርድ ቤት፤ የአማፂ ቡድኑ አዛዥ መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ጨምሮ 201 ተከሳሾች ላይ "ጦርነት በመቀስቀስ እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማናጋት" ወንጀል በዚህ ሳምንት ችሎት እንደከፈተባቸው ተገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0