የእንዶዴ ደረቅ ወደብ የ610 ሚሊዮን ብር ማስፋፊያ ጭነት የማስተናገድ አቅሙን በሦስት እጥፍ እንደሚያሳድግ ተገለፀ
17:55 25.01.2026 (የተሻሻለ: 18:04 25.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የእንዶዴ ደረቅ ወደብ የ610 ሚሊዮን ብር ማስፋፊያ ጭነት የማስተናገድ አቅሙን በሦስት እጥፍ እንደሚያሳድግ ተገለፀ
በወደቡ የከባድ ጭነት ማመላለሻ ግቢ ንጣፍ ላይ በሚካሄደው ማስፋፊያ፤ ጭነት የማስተናገድ አቅሙ ቀደም ሲል ከነበረበት 1 ሺህ ጭነቶች ወደ 4 ሺህ ለማሳደግ ታቅዷል።
⏳ ከተጀመረ ሁለት ወራት ያስቆጠረው ግንባታ በአሁኑ ወቅት 62.5 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሷል።
⏰ በእንዶዴ የጭነት ግቢ ቀደም ሲል ከ10 እስከ 12 ሰዓታት ይፈጅ የነበረው የመጫን እና የማውረድ ሂደት ወደ ሁለት ሰዓት ዝቅ ይላል መባሉን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚመራና የሚገነባ ነው።
እንዶዴ የደረቅ ወደብ የአዲስ አበባ-ጂቡቲ የባቡር መስመርን ከዋና ዋና የኢንዱስትሪ ዞኖች ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ የትራንስፖርት ትስስር ማዕከል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X