ግብፃዊቷ ጸሐፊ የመጀመሪያውን የብሪክስ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት አሸነፉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱግብፃዊቷ ጸሐፊ የመጀመሪያውን የብሪክስ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት አሸነፉ
ግብፃዊቷ ጸሐፊ የመጀመሪያውን የብሪክስ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት አሸነፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.01.2026
ሰብስክራይብ

ግብፃዊቷ ጸሐፊ የመጀመሪያውን የብሪክስ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት አሸነፉ

ደራሲዋ ሳልዋ ባክር በ2026 የካይሮ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ ላይ በተካሄደው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውን የብሪክስ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት ተሸላሚ እንደሆኑ የስፑትኒክ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

የጸሐፊዋ አሸናፊነት ዓለም አቀፍ ዳኞች ከመከሩበት በኋላ በሩሲያ ካባሮቭስክ ከተማ እ.ኤ.አ ኅዳር 30 ቀን 2025 በይፋ መገለጹ ይታወሳል።

"የዚህ ሽልማት የመጀመሪያ አሸናፊ በመሆኔ ደስታ እና ኩራት ይሰማኛል" ሲሉ ጸሐፊዋ ሽልማቱን ሲረከቡ ተናግረዋል።

"ይህ ሽልማት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ካሉ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማቶች የተለየ ጥልቅ ራዕይ ያለው ነው። ምክንያቱም ብሪክስ ከምንም በላይ ለበርካታ አስርት ዓመታት ዓለም አቀፋዊ ሰብዓዊ ባሕልን ለመቅረጽ ሲረዳ የቆየ የሥልጣኔ ኅብረት ነው" ሲሉ ባክር አክለው ገልጸዋል።

🪶 እ.ኤ.አ በኅዳር 2024 ሞስኮ በተካሄደው የብሪክስ ፎረም ላይ የተመሠረተው ይህ ሽልማት፤ የኅብረቱን አባል ሀገራት ሥነ-ጽሑፍ ለማስተዋወቅ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለእነዚህ ሀገራት የባሕል ሀብት ትኩረት እንዲሰጥ ለማድረግ ያለመ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0