ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት በሀገር ውስጥ አመረተች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 3
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 3 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት በሀገር ውስጥ አመረተች

በግማሽ ዓመቱ 204 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ምርት ለውጪ ገበያ ማቅረብ እንደቻለችም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነቃቃ በማድረጉ የማምረት ዐቅም ባለፈው ዓመት ከነበረበት የ46 በመቶ ምጣኔ ዘንድሮ ወደ 66 በመቶ ማደጉን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ161 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውንም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0