የወቅቱ ተራ የአውሮፓ የፖለቲከኞች ትውልድ የትራምፕን ጫና መቋቋም አይችልም - ክሬምሊን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየወቅቱ ተራ የአውሮፓ የፖለቲከኞች ትውልድ የትራምፕን ጫና መቋቋም አይችልም - ክሬምሊን
የወቅቱ ተራ የአውሮፓ የፖለቲከኞች ትውልድ የትራምፕን ጫና መቋቋም አይችልም - ክሬምሊን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.01.2026
ሰብስክራይብ

የወቅቱ ተራ የአውሮፓ የፖለቲከኞች ትውልድ የትራምፕን ጫና መቋቋም አይችልም - ክሬምሊን

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል፦

ስለ አውሮፓ አመራር፦ "የወቅቱ ተራ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ትውልድ የዶናልድ ትራምፕን ጥንካሬ መቋቋም የማይችል እና በድርብ መስፈርት የታመሰ ነው።"

በአሜሪካ እና አውሮፓ መካከል ስላለው ውጥረት፦ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው መቃቃር ለዓመታት በአውሮፓ በኩል ሲታይ የነበረው ግብዝነት ውጤት መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ "አውሮፓ ትራምፕ ከማክሮን ጋር ያደረጉትን ንግግር ይፋ በማድረጋቸው ተቆጥቷል፤ ነገር ግን ማክሮን ከፑቲን ጋር ያደረጉትን ንግግር ይፋ ባደረጉ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ተቃውሞ አላሳየም" ብለዋል።

ስለ ትራምፕ አካሄድ፦ ትራምፕ ችግሮችን በኃይል ለመፍታት የሚሞክሩበትን መንገድ፤ "በጉልበት አንገትን ማስደፋት" በሚለው የሩሲያውያን የፈሊጥ አነጋገር ገልጸውታል።

የሩሲያ አቋም፦ "የሚንበረከኩ መንበርከካቸውን ይቀጥላሉ፤ ዋናው ቁምነገር ግን ሩሲያ አለመንበርከኳ ነው።"

ስለ ዓለም አቀፍ ሥርዓት፦ የትራምፕ ታክቲኮች አንዳንዴ ሩሲያ ከምታራምደው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም እይታ ጋር አይጣጣሙም።

ስለ ወቅታዊው ሁኔታ፦ "ዓለም በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጣለች፤ አሁንም የለውጥ ሂደቷን እንደቀጠለች ነው።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0