ጅግጅጋ ከተማ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም ሙሉ በሙሉ አቆመች
14:06 25.01.2026 (የተሻሻለ: 14:14 25.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጅግጅጋ ከተማ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም ሙሉ በሙሉ አቆመች
የሶማሌ ክልል መዲና የፕላስቲክ ከረጢቶችን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በወረቀትና በጨርቅ በተሠሩ ተኪ ምርቶች አገልግሎት እንዳስጀመረች ተሰማቷል፡፡
ውሳኔው በሀገር አቀፍ ደረጃ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የተያዘውን አቅጣጫ መነሻ ያደረገ መሆኑን የሶማሌ ክልል የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሙሄዲን አብዲ ሁሴን (ኢ/ር) አስታውቀዋል።
የፕላስቲክ ፌስታሎችን ከአገልግሎት የማስወገድ ሥራው በቀጣይም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በክልሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎችን የሚተኩ ምርቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን ለመገንባት መታቀዱን የገለጹት ኃላፊው፤ ባለሀብቶችና ኢንቨስተሮች በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X