ጊኒ ቢሳው አወዛጋቢውንና በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄደው የክትባት ሙከራ መታገዱን አረጋጠች

ጊኒ ቢሳው አወዛጋቢውንና በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄደው የክትባት ሙከራ መታገዱን አረጋጠች
የጊኒ ቢሳው የጤና ሚኒስትር ኪንሂን ናንቶቴ፤ ውሳኔው የተላለፈው የሕክምና ሥነ-ምግባር ኮሚቴ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት "የሄፓታይተስ ቢ" ክትባት ሙከራ ሳይንሳዊ ይዘት በትክክል አልተገመገመም ማለቱን ተከትሎ እንደሆነ ገልጸዋል።
በክትባት ሙከራው ከ14 ሺህ አራስ ልጆች ለግማሾቹ የሚሰጠውን የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ለማዘግየት ታቅዶ ነበር። ይህም ክትባቱ ወዲያውኑ መሰጠት አለበት ከሚለው የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ ጋር የተቃረነ ሲሆን ወደ 20 በመቶ የሚጠጉ አዋቂዎች በቫይረሱ በሚጠቁባት ሀገር ውስጥ የሥነ-ምግባር ስጋትን አስነስቷል።
መጀመሪያ ለጥናቱ ፍቃድ ሰጥቶ የነበረው የጊኒ የሥነ-ምግባር ኮሚቴ፤ ክትባቱን ለመከልከል ቁልፍ መረጃዎች በትክክል አልቀረቡም ብሏል። ማንኛውም የተሻሻለ የሙከራ እቅድ የመንግሥትን ሙሉ ፍቃድ ማግኘት እንደሚኖርበትም ኮሚቴው አመልክቷል።
የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ባለፈው ሳምንት "ይህ የሀገሪቱ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው" በማለት የጊኒ ቢሳውን ውሳኔ ደግፈዋል።
ይህም ቀደም ሲል የክትባት ሙከራው ይቀጥላል ካሉት የአሜሪካ የጤና ባለሥልጣናት ጋር ይቃረናል።
አፍሪካ ሲዲሲ የጥናቱን ይዘት በመገምገም ረገድ ለጊኒ ቢሳው ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X