የአፍሪካ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ከፊች የደረጃ መዳቢ ተቋም ጋር ያለውን ግንኙነት በይፋ ማቋረጡን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ከፊች የደረጃ መዳቢ ተቋም ጋር ያለውን ግንኙነት በይፋ ማቋረጡን አስታወቀ
የአፍሪካ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ከፊች የደረጃ መዳቢ ተቋም ጋር ያለውን ግንኙነት በይፋ ማቋረጡን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.01.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ከፊች የደረጃ መዳቢ ተቋም ጋር ያለውን ግንኙነት በይፋ ማቋረጡን አስታወቀ

​ መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው አፍሬኤግዚም ውሳኔው የተላለፈው ከግምገማ በኋላ እና የፊች የደረጃ አሰጣጥ ሂደት የባንኩን የመመስረቻ ስምምነት እና ተልዕኮ "በሚገባ እንደማይረዳ" "ጽኑ እምነት" ስላለው እንደሆነ ገልጿል።

​እርምጃው ባንኩ "ቅድሚያ በሚሰጠው የአበዳሪነት ደረጃ" ዙሪያ ለአንድ ዓመት ከዘለቀ አለመግባባት በኋላ የተወሰደ ነው። ይህ ደረጃ በተለምዶ እንደ አይኤምኤፍ ያሉ አበዳሪ ተቋማት፤ ሀገራት የዕዳ ሽግሽግ በሚያደርጉበት ወቅት ከኪሳራ የሚጠበቁበት አሠራር ነው።

​ የአሜሪካ የክሬዲት ደረጃ መዳቢ ተቋም ፊች፤ በከፍተኛ የብድር ስጋት በቅርቡ የባንኩን የመበደር አቅም ወደ "አሉታዊ" ዝቅ አድርጓል። ተቋሙ ባንኩ እንደ ጋና እና ዛምቢያ ላሉ ዕዳቸውን መክፈል ላልቻሉ የአፍሪካ ሀገራት በሰጠው የብድር ሽግሽግ ዙሪያ ጥያቄ አንስቷል።

ባንኩ በበኩሉ "የአፍሬኤግዚም ባንክ የንግድ ሁኔታ በባለአክሲዮኖች ጠንካራ ግንኙነት እና በ53 አባል ሀገራት ተፈርሞ በጸደቀው የመመስረቻ ስምምነት ውስጥ በተቀመጡ የሕግ ጥበቃዎች ተደግፎ አሁንም ጠንካራ ነው" ብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0