የአቡ ዳቢ የዩክሬን ድርድር ባልተቋጩ የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር - የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአቡ ዳቢ የዩክሬን ድርድር ባልተቋጩ የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር - የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የአቡ ዳቢ የዩክሬን ድርድር ባልተቋጩ የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር - የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.01.2026
ሰብስክራይብ

የአቡ ዳቢ የዩክሬን ድርድር ባልተቋጩ የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር - የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ስፑትኒክ ያገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​▪ የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን በአቡ ዳቢ ከአሜሪካ ጋር በተደረገው የሦስትዮሽ ውይይት ከዚህ በፊት በተለየ ቀጥተኛ ግንኙነት አድርገዋል።

​▪ ለሁለት ቀናት የቆየው ድርድር “በገንቢ እና አዎንታዊ መንፈስ” ተካሂዷል።

​▪ ውይይቶቹ ትኩረታቸውን ያደረጉት አሜሪካ ባቀረበችው የሰላም ማዕቀፍ እልባት ባላገኙ ነጥቦች ላይ እና ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚያግዙ የጋራ መተማመኛ እርምጃዎች ላይ ነው።

​▪ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግጭቶች ያለ ውይይት ሊፈቱ እንደማይችሉ አጽንኦት በመስጠት ለዓለም አቀፍ የግጭት አፈታት ጥረቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ቃል ገብታለች።

​▪ዶናልድ ትራምፕ ድርድሩ እንዲመቻች ላደረጉት ሚና አድናቆቷን ገልጻለች።

ስብሰባዎቹ አዲስ በተቋቋመው የሩሲያ-አሜሪካ-ዩክሬን የሦስትዮሽ የደህንነት ጉዳዮች የሥራ ቡድን የተካሄው የመጀመሪያው ነው። ቡድኑ በአድሚራል ኢጎር ኮስቲዩኮቭ የሚመሩ ከፍተኛ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን አካቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0