ተመራማሪው “የአረቢካ ቡና" የሚለው ስያሜ “የኢትዮጵያ ቡና” ተብሎ እንዲቀየር ምክረ ሃሳብ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱተመራማሪው “የአረቢካ ቡና" የሚለው ስያሜ “የኢትዮጵያ ቡና” ተብሎ እንዲቀየር ምክረ ሃሳብ አቀረቡ
ተመራማሪው “የአረቢካ ቡና የሚለው ስያሜ “የኢትዮጵያ ቡና” ተብሎ እንዲቀየር ምክረ ሃሳብ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.01.2026
ሰብስክራይብ

ተመራማሪው “የአረቢካ ቡና" የሚለው ስያሜ “የኢትዮጵያ ቡና” ተብሎ እንዲቀየር ምክረ ሃሳብ አቀረቡ

​ኢትዮጵያ የቡና መገኛ በመሆኗ ለታሪክና ለሳይንሳዊ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት የስያሜ ለውጥ እንዲደረግ ተመራማሪው ሰሎሞን ተክሌ ጥሪ አቅርበዋል።

መገኛው ኢትዮጵያ የሆነው “አረቢካ ቡና” እውነተኛ ምንጩን የሚያንፀባርቅ ስያሜ ያስፈልገዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ሌሎች ሀገራት የቡና መገኛ ነን በማለት የሚያቀርቡትን መረጃ አልባ መከራከሪያ ነቅፈዋል።

ተመራማሪው በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ የቡና መገኛ መሆኗን በሳይንሳዊ መንገድ በማረጋገጥ በዩኔስኮ እውቅና ለማስገኘት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

"ታሪካዊ እና ሳይንሳዊ ምንጮች ቡና ከኢትዮጵያ የተገኘ መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ" ሲሉ ተመራማሪው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0