የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ለወንድማቸው አዲስ ሹመት በመስጠት አዲስ መንግሥት አዋቀሩ
17:32 24.01.2026 (የተሻሻለ: 17:34 24.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ለወንድማቸው አዲስ ሹመት በመስጠት አዲስ መንግሥት አዋቀሩ
አዲሱ ካቢኔ 34 ሚኒስትሮችን እንዳቀፈ አላሳን ዋታራ ያፀደቁት አዋጅ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ቤግሬ ማምቤ ከጥቂት ቀናት በፊት በድጋሚ ተሹመዋል።
ዋና ዋና ለውጦች፦
🟠 የፕሬዚዳንቱ ታናሽ ወንድም ቴኔ ቢራሂማ ዋታራ የመከላከያ ሚኒስትርነታቸውን ከማስጠበቅ ባለፈ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል።
🟠 ኒያሌ ካባ የቀድሞውን ሚኒስትር ሌዎን ካኩ አዶምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ተረክበዋል።
▪ አብዛኞቹ ኃላፊነቶች አልተለወጡም፦ የሀገር ውስጥ እና ደኅንነት፣ የፍትሕ፣ እንዲሁም የበጀት ሚኒስትሮችን ጨምሮ አንጋፋ ሚኒስትሮች በነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ላይ ቀጥለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X