“ለኢትዮጵያ የቡና ምርታማነት የፋይናንስ አቅርቦት ዋነኛው ችግር ሆኗል” በሚል የዓለም ባንክ ከሠሞኑ ይፋ ያደረገው ጥናት የተጋነነ ነው - የኢትዮጵያ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን
17:13 24.01.2026 (የተሻሻለ: 20:44 24.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ለኢትዮጵያ የቡና ምርታማነት የፋይናንስ አቅርቦት ዋነኛው ችግር ሆኗል” በሚል የዓለም ባንክ ከሠሞኑ ይፋ ያደረገው ጥናት የተጋነነ ነው - የኢትዮጵያ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን
ባንኩ የቡና ምርታማነት እንዳይሻሻል የፋይናንስ አቅርቦት 90 በመቶ ድርሻ እንዳለው የጠቆመበት ጥናት የሚመለከተውን ትክክለኛ ተቋም መረጃ እንዳላካተተ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
የፋይናንስ አቅርቦት ችግር በዋናነት የሚገጥማቸው ቡና አምራች አርሶ አደሮች መሆናቸውን ጠቅሶ፤ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለአርሶ አደሮቹ ያለ ምንም ማስያዣ ባላቸው መሬት ልክ ብድር የሚሰጣቸው ባንክ እንዲቋቋም መደረጉን አመላክቷል።
የዓለም ባንክ ጥናት የቡና ምርታማነት እንዳይሻሻል ምክንያት ናቸው ያላቸው መስኮች፦
የፋይናንስ አቅርቦት 90%፣
ትራንስፖርት 51%
የመሠረተ ልማት ተቋማት ችግር 13%።
በትራንስፖርት በኩል ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቡናን በባቡር ማጓጓዝ እንደተጀመረ ባለሥልጣኑ አስታውቋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X